ሃገረ ስብከቱ በአሁኑ ሰዓት የዋሽንግተን የኦሪገን እና አይዳሆ እና አካባቢው ሃገረ ስብከትን የያዘ ሲሆን በስሩም ፲፭ አቢያተ ክርስቲያናትን ፣ ፩ ገዳም፣ ፲፭ የሰንበት ት/ቤቶችን እና ፬ ታላላቅ ማህበራትን ይዟል።
ራዕያችን
በሀገረ ስብከታችን ያስቀመጠውን ራዕይ ለማሳከት የሥራ አስፈፃሚ ክፍሎችን በማስተባበር፣ በማደራጀት፣ ሕጎችንና ውስጠ ደንቦችን በመከታተል እንዲሁም በማስፈጽም የቤተክርስቲያንቱን መልካም አገልግሎት ለምእመናን ማዳረስ
ተልዕኳችን
ስብከተ ወንጌል ተልዕኮ
በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በሚረዱትና በሚገባቸው ቋንቋ ስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ማዳረስና ምእመናኑ ሃይማኖታችውንና የቤተክርስቲያንቱን አስተምህሮ ተረድተው ወደ ቅዱስ ቁርባኑ እንዲቀርቡ ማድረግ
ትምህርት እና ስልጠና ክፍል ተልዕኮ
ውጤታማ የትምህርትና ሥልጠና ዘዴዎችን በመጠቀም እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በጥራት ተዘጋጅተው የመንፈስ የአእምሮ እና የአካል ዕድገትን የሚያጎናጽፉ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሙያ እና የሕይወት ክሂሎት ትምህርቶችና ሥልጠናዎችን ለሀገረ ስብከታችን አገልጋዮች እና ምእመናን እንዲቀርብ ማድረግ፣
የሰንበት ት/ቤት ተልዕኮ
በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሚገኙን የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሰንበት ትምህርቶችን በማስተባበር ወጣቶች በቤተክርስቲያን አገልግሎት ንቁ ተሳትፎ እንድኖራቸውና ወጥ የሆነ አገልግሎት የሚሰጡና፣ የቤተ ክርስቲያናቸውን ሕግና ሥርዓት የሚያቁ ለሃይማኖታቸው ቀናይ የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት፣
የካህናት አገልግሎት ክፍል ተልዕኮ
Moreየአገልግሎት ሃላፊዎች
![profile6 የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile6-280x280.jpg)
![መልአከ አሚን ዶ/ር ቀሲስ ፋሲል አስረስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile3-210x210.jpg)
![ሊቀ ትጉሃን ጌታቸው የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile8-210x210.jpg)
![መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም የሀገረ ስብከቱ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile1-170x170.jpg)
![መልአከ ሰላም ቀሲስ ክብሩ የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ኃላፊ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile2-170x170.jpg)
![የትምህርትና የስልጠና መምሪያ ኃላፊ መምህር ልዑለ ቃል ዓለሙ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile4-170x170.jpg)
![መልአከ ብርሃናት ቀሲስ መኮንን የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile9-170x170.jpg)
![መልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለም የሰንበት ትምህርት ቤት መምሪያ ኃላፊ ከፖርትላንድ ኦሪገን](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/profile5-170x170.jpg)
![ቀሲስ አስተዋይ የሀገረ ስብከታችን የልማት ክፍል ኃላፊ](https://wa.eotcus.org/wp-content/uploads/2021/07/photo_2021-07-11_23-33-41-1-170x170.jpg)